ትምህርት ቤቷ ቤተ መጻሕፍቱን በስሟ ሰይሞላት ነበር፤ ዘንድሮ ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ከፍተኛውን… — Temari — TG.ME

🇪🇹 ትምህርት ቤቷ ቤተ መጻሕፍቱን በስሟ ሰይሞላት ነበር፤ ዘንድሮ ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ከፍተኛውን ውጤት አስመዘገበች! 🏆

በአማራ ክልል፣ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በሚገኘው እንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ህዳሴ ዘመኑ፣ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ 583.03 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግባለች። 🇪🇹

ይህ ግን ስሟ በስኬት ሲጠራ የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። ❤️

ከ11ኛ ወደ 12ኛ ክፍል ስትሸጋገር 99.67% አማካይ ውጤት በማስመዝገቧ፣ ትምህርት ቤቷ ቤተ መጻሕፍቱን “ህዳሴ ላይብረሪ” በማለት በስሟ ሰይሞት ነበር። 📚

እነዚህ ሁለቱ ውጤቶች የተለያዩ ስኬቶችን የሚያሳዩ ናቸው፤ 99.67% የአንድ ዓመት የክፍል ውስጥ ትምህርት ውጤቷ ሲሆን፣ 583.03 ደግሞ በሀገር አቀፍ ፈተና ያገኘችው ነጥብ ነው። ሁለቱም ግን የህዳሴ ድንቅ ውጤቶች ናቸው። 👏

ስለ ህዳሴ ተጨማሪ መረጃ፦
https://temari.et/am/news/grade-12-2018-ec-second-highest-scorer
🔥8❤3
August 25, 2026 783 1