ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ!!!! የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ… — Temari — TG.ME

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ!!!!

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

(የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ)

- ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት።

- ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን  550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው።

- ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው።

- ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል።

- ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል።

በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ?

- በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው።

- የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ?

በተፈጥሮ ሳይንስ
🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ
🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ

በማህበራዊ ሳንይንስ
🥇 ከወንድ 👉  576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት

-  ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል።

📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል።

አዲስ አበባ
ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም
❤5🔥2
August 23, 2026 971 1