የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 23 ጀምሮ ይሰጣል።
ዘንድሮ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል።
ፈተናው በበይነ መረብ እና በወረቀት የሚሰጥ ሲሆን፤ ፈተናውን በበይነ መረብ በ6 ዙር የሚወስዱ ተማሪዎች በሲስተሙ ላይ ልምምድ አድርገዋል።
የተፈጥሮ ሳይንስ የወረቀት ተፈታኞች በ3ኛው ዙር ከሐምሌ 1 እስከ 3 ድረስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ የወረቀት ተፈታኞች ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።
በ714 ትምህርት ቤቶች ወይም ማዕከላት ላይ የሚገኙ ከ114 ሺህ በላይ ኮምፒዩተሮችን የመለየት ስራ ተካሂዶ የፈተና ስርዓቱን፣ መሰረተ ልማቱን እና የኃይል አማራጮችን ታሳቢ በማድረግ አሁን 607 ማዕከላት ተዘጋጅተዋል።
በዩኒቨርሲቲዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆችን ጨምሮ በተለያዩ ማዕከላት ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተማሪዎች ስማርት ሰዓት፣ የሞባይል ስልክ፣ የጆሮ ማዳመጫ (ኤርፎን)፣ ድምጽና ምስል የሚቀዱ ነገሮችን መያዝ ከፈተና ስለሚያሳግድ አጥብቆ የተከለከለ ነው።
8
2June 30, 2026 2.8K


