በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች (በተለይም በMinnesota፣ Georgia እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች) የሚገኙ… — Tech Byte prompt — TG.ME

በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች (በተለይም በMinnesota፣ Georgia እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች) የሚገኙ የህዝብ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ጣቢያዎች በኢራን የሃከር ቡድኖች ከባድ የሳይበር ጥቃት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።
CISA፣ FBIና EPA ባወጡት የጋራ መግለጫ  አብዛኞቹ አነስተኛ የከተማ ውሃ ጣቢያዎች የውሃ ፍሰቱንና ግፊቱን ለመቆጣጠር እንደ PLCs (Programmable Logic Controllers) እና HMIs (Human Machine Interfaces) የመሳሰሉ ኦፕሬሽናል ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው ጥቃቱን እንዳደረሱ ገልፀዋል።
እነዚህ መሳሪያዎች በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ስለሆኑና ደካማ የይልፍ ቃል የሚጠቀሙ በመሆናቸው ሃከሮቹ በቀላሉ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
ሃከሮቹ ሲስተሙ ውስጥ ከገቡ በኋላ የትዕዛዝ መቆጣጠሪያ ፓስወርዶችን በመቀየር የውሃ ግፊት መቆጣጠሪያዎችንና ሴንሰሮችን በማበላሸት አጠቃላይ ሂደቱን አስተጓጉለውታል። ጥቃቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች የውሃ ግፊት ቀንሶ ታይቷል።

በርካታ የውሃ ጣቢያዎች የኢንተርኔት ሲስተማቸውን አጥፍተው ወደ ድሮው በእጅ የመቆጣጠር (Manual Mode) አሰራር እንዲመለሱ ተገደዋል።

የአሜሪካ የደህንነት ተቋማት የጥቃቱን አፈጻጸምና የሃከሮቹን አሰራር (Signature) በማየት ከኢራን መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደ Handalaና IRGC የተሰኙ ቡድኖች እንደሆኑ ገምተዋል። ኢራን ቀደም ሲል በ2023 በPennsylvania የውሃ ጣቢያዎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽማ እንደነበር ይታወሳል።
August 15, 2026 19