Googleን የሚያሰጋው አዲሱ የ AI ቴክኖሎጂ! (SearchGPT መጣ) 🌐 ሰላም ቤተሰቦች! የዛሬው ትኩስ… — Tech Byte prompt — TG.ME

🚨 Google የሚያሰጋው አዲሱ AI ቴክኖሎጂ! (SearchGPT መጣ) 🌐
ሰላም ቤተሰቦች! የዛሬው ትኩስ የቴክኖሎጂ ዜናችን የዓለማችንን ትልቁን ኩባንያ Googleን እንቅልፍ ስለነሳው አዲስ ቴክኖሎጂ ነው።
የ ChatGPT ፈጣሪ የሆነው ታዋቂው OpenAI ኩባንያ፣ "SearchGPT" የተባለ አዲስ እና እጅግ ዘመናዊ የ Search Engine (መፈለጊያ) ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል።
SearchGPT Google በምን ይለያል?
እስካሁን Google ላይ አንድ ነገር ስንፈልግ፣ ከመልሱ ይልቅ በርካታ የ Website ሊንኮችን እና ማስታወቂያዎችን ነው የሚደረድርልን። አዲሱ SearchGPT ግን ልክ እንደ ሰው ጥያቄያችንን ተረድቶ፣ ትክክለኛውን እና የተብራራ መልስ ከተለያዩ ድረ-ገጾች አሰባስቦ ከነ ምንጩ (Source) በቀጥታ ያቀርብልናል።
ይህ የ AI ቴክኖሎጂ መረጃ የምንፈልግበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ ስለሚቀይረው፣ ብዙ የቴክኖሎጂ ተንታኞች የ Googleን የዓመታት የበላይነት ሊያናጋው እንደሚችል እያወሩ ይገኛሉ።
❤1
August 28, 2026 8