ን እያሳደግን ለራሳችን ከየት ጊዜ እናግኘ " ብላ ስትመልስለኝ ዝም አልኩ ። " ውይይ………ወንዶች!!! " አሉ ሴቶች ። ሳላድግ ማግባት አልፈለግም አላገባም ። አላገባም የምለው ትዳርን ጠልቼ አደለም ፣ ፈሪም ስለሆነኩም አደለም ፣ ሊያገባ ያሰበን ሀሳብ ለማስቀየርም አደለም ። አላገባም የምለው ለምን እንደማገባ እስኪገባኝ ነው ። ስለ አላህ ተረድቶና አውቆ በሚያመልከውና በጭፍን በሚያመልከው መሀል ልዩነት እንዳለ ሁሉ ለምን እንደሚያገባ ገብቶት ያገባና ለምን እንደሚያገባ ሳይገባው ባገባ ሰው መሀል ልዩነት አለ ። ፍቺው በዝቶ የትዳር ጉጉቱ የቀነሰው ለምን እንዳገቡ ባልገባቸው ተጋቢዎች ምክንያት ነው ። ለምን እንዳገቡ ገብቷቸው የተጋቡ ፣ ሳይገባቸው ተጋብተው እንዲገባቸው የሚሞክሩ ፣ ጭራሹን አልገባኝም ብለው እንዲገባቸው የማይፈልጉ በሁላችንም ሂወት ውስጥ ሁለት ተጋቢዎች አሉ እኛ ለመገኘታችን ሰበብ የሆኑ ። ሁላችንም ስናገባ ምክንያት ይኖረናል ነገር ግን ለምን እንደምናገባ ይግባን ። መስመሩን ካልሳተ ምከንያታዊነት ከስህተት ይታደጋል ። ትዳራቸው ያማረና ስኬታማ ነው ብለን እንደ አርአያ የምንጠራቸውና የምንዘክራቸው ለምን እንዳገቡ የገባቸው ናቸው ። ለምን እንደምናገባ ሳይገባን ትዳር አናንቋሽሽ!!! ለምን እንደምናገባ ይግባን ። ካልተረዳነው ያወቅነው አይጠቅመንም ጥፋት እንጂ ሌላ አይፈይድልንም ። ሁላችሁም አግቡ ነገር ግን ቅድሚያ ለምን እንደምታገቡ ይግባቹህ ። ገብቷቹህ ያገባቹህ ያልገባውን ገስፁ ። ሳይገባቹህ ያገባቹህ ደሞ ምክንያታቹን ፈልጋቹህ ከፍቺ እራሳቹን ታደጉ ። መረዳት ከድርጊት ይቀድማል ። ድርጊት ከመረዳት ከቀደመ ጥፋት ያስከትላል ። እኔ ለምን እንደማገባ በደንብ ሲገባኝ አገባለው ካልገባኝ ግን አላገባም ። እደግመዋለው ለምን እንደማገባ ሳይገባኝ አላገባም ። . "በቀለም ጠብታ፣ማንነት ሲረታ!"
የጥበብ ቤት: post #679 — TG.ME
February 28, 2020 6.2K 37