ሴትነት በኮሜንቶች ስር! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ • የሴትነት ክብር - በየ ኮሜንቱ ስር፤ • ጥፍጥናውን ትቶ… — Sunnah Path — TG.ME

🚫 ሴትነት በኮሜንቶች ስር!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

• የሴትነት ክብር - በየ ኮሜንቱ ስር፤
• ጥፍጥናውን ትቶ - እንደ እሬት ሲመር፤
• መስፈሪያውን ስቶ - እንደ ቁራ ሲበር፤
• መቀመጫን ለቆ - በጎዳና ሲያድር፤
• መኖሪያውን ርቆ - በየሚዲያው ሲዞር፣
• በጣም ያሳዝናል - ያስኮንናል የምር፤
• ሰምተነው አናቅም - ከደጋጎች ሰፈር፤
• ታይቶም አይታወቅ - ከቅኖቹ መንደር፤
▬▬▬▬▬▬▬▬
• አይናፋሯ እንስት - ሐያእን ስታፈርጥ፤
• በየ ኮሜንቱ ስር - ለመፃፍ ስትሮጥ፤
• ካገኘችው ሁሉ - መልስ ስትሰጣጥ፤
• አድ አድርገዋት - እፍረቷ ሲመጠጥ፤
• ራሷም አድ አድርጋ - ክብሯን ስትረግጥ፤
• በግል እያዋራች - እሳት ስታጨበጥ፤
• ባሏን ችላ ብላ - በሚዲያ ስትማግጥ፤
• ከአጅነቢይ ጋር - በድፍረት ስትዘንጥ፤
▬▬▬▬▬▬▬▬
• አቤት ሲዘገንን  - አቤት ሲሰቀጥጥ፤
• ማየት አይስችልም - ንዴትም አያስውጥ፤
• ሴቶችን ፈታኝ ሆይ - ማጃጃሉን አቋርጥ፤
• መልከስከሱን ትተህ - አቅጣጫህን ለውጥ፤
• ጌታችን ፊት ቀርበህ - በጥያቄ ሳትፈጥ፤
• ማምለጫ የለምና - አይገኝም ማምለጥ፤
• መናገር ይሻላል - ዝም ቦሎ ከማፍጥ፤
▬▬▬▬▬▬▬▬

👉👇
https://t.me/Sunnah_Path1/2810
👍2
August 27, 2026 67