✍
የዩሱፍ ብስለትና ስነምግባር ተመልከት.......
📖{...وَقَدْ أَحْسَنَ بِىٓ إِذْ أَخْرَجَنِى مِنَ ٱلسِّجْنِ وَجَآءَ بِكُم مِّنَ ٱلْبَدْوِ مِنۢ بَعْدِ أَن نَّزَغَ ٱلشَّيْطَٰنُ بَيْنِى وَبَيْنَ إِخْوَتِىٓ ۚ إِنَّ رَبِّى لَطِيفٌۭ لِّمَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ}
{...ጌታዬ ከወህኒ ቤት ባወጣኝና ሰይጣንም በእኔና በወንድሞቼ መካከል ካበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ በእርግጥ ለእኔ መልካም ዋለልኝ፡፡ ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው፡፡ እነሆ እሱ ዐዋቂው ጥበበኛው ነው" አለ፡፡}
[ዩሱፍ:¹⁰⁰]
ዩሱፍን ያሳሰሩት ወንድሞቹ ሳይሆኑ የንጉሱ ሚስት ነበረች። ወንድሞቹ ያደረጉት እሱን ጉድጓድ ውስጥ መጨመር ነበር። ዩሱፍ ግን አባቱንና ወንድሞቹን ተሰብስበው በመጡ ጊዜ አላህ የዋለለትን ውለታ ሲጠቅስ ያወሳው ከወህኒ ቤት መውጣቱን እንጂ ከጉድጓድ መውጣቱን አልጠቀሰም።
ምክንያቱም፦
ከጉድጓድ የመውጣቱን ፀጋ ቢጠቅስ: ወደ ጉድጓዱ የወረወሩት ወንድሞቹ ክስተቱን አስታውሰው ልባቸው ሊጣበብ ይችላል። በመሆኑም የጉድጓዱን ዘለለና በሌላ ሰው ሰበብ የተከሰተበት የወህኒ ቤቱ ጉዳይ አወሳ።
https://t.me/Sunnah_Path1/2805
August 26, 2026 84