Good Morning GM ➡️ዛሬም እንደተለመደው ከስኬታማ ሰዎች ያገኘናቸውን 3 ጠቃሚ ልምዶች እና ሃሳቦች… — TRADE INSIGHT AIRDROP — TG.ME

Good Morning GM ➡️ዛሬም እንደተለመደው ከስኬታማ ሰዎች ያገኘናቸውን 3 ጠቃሚ ልምዶች እና ሃሳቦች እናጋራቹ። ➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️ 1️⃣ ህልም ያለ ስራ ሕልም ብቻ ነው! እቅድ ኖሮህ ሕልም አልመህ በደምብ ካልሰራህ ለምን አልተሳካልኝም ማለቱ ጥቅም አይኖረውም! የስኬት ጫፍ ላይ እስክትደርስ ድረስ በደምብ መስራት አለብህ! አንዳንዴ አንተን መርዳት የሚችለው ብቸኛው ሰው አንተው ራስህ ነህ! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 2️⃣በህይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰም ነው። የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም። ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት። ስኬት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከሌሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 3️⃣በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን ተመኝ፤ መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት! Have Nice Day

🔥6👍2👏2
December 20, 2024 249