ይህን ላደረገ ሃሌ ሉያ
ውድ ምዕመናን ሰንበት ትምህርት ቤታችን በ40ኛ አመት ጉዞዋ ከነፈተናዎቻችንና ድክመቶቻችን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነን ግዴታዎቻችንን ተወጥተን በዘንድሮ አመት ሃገር አቀፍ የምስጋና የደም ለጋሾች ቀን መርሐግብር በሁለተኝነት ደረጃ አሸናፊ የሆንን ሲሆን ከአማኑኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር በድምር አንደኛ ሆና ቤተክርስቲያናችን የቀደመውን በመንግስታት ሳይቀር የማትጠቅም ነች የሚለውን ትርክት ወደ ለአገሯ ዜጎች ተደራሽ ተቋምነት ዳግማዊ የዚህ ዘመን በጎ ታሪክ ባለቤትነት ማሳያ የሚቀይር ታላቅ ስራን ማከናወን ተችሏል። በዚህም ሰንበት ትምህርት ቤታችንና ሃይማኖታችሁን በማይጠፋ የታሪክ የምስጋና ሰነድ ማስፈር ችላችዋል እንኳን ደስ አላችሁ
በርቱ ፅኑ በሃይማኖት ቁሙ !







