ስመ ጥሩው የሥራ መሪ የነበሩት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የአቤት ሆስፒታል ዋና ሥራ… — St.Paul's Hospital Millennium Medical College — TG.ME

ስመ ጥሩው የሥራ መሪ የነበሩት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የአቤት ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የ ዶር ጸጋይ ገብረ አናንያ ድንገተኛ ህልፈትን አስመልክቶ በሥራ ባልደረቦቻቸውና በወዳጆቻቸው የተዘጋጀ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ:

ዶ/ር ጸጋይ ገብረ አናንያ በአጭር ጊዜ የአቤት ሆስፒታልን ወደ ላቀ የሕክምና ማዕከል ለማሸጋገር በርካታ የለውጥ ሥራዎችን አከናውነዋል። በመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓቱ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅና የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎችና የሥራ ባልደረቦቻቸው በአመራራቸው የተመዘገቡ ጉልህ ለውጦችን፣ ለሥራ ያላቸውን ቁርጠኝነትና ስለመልካም ምግባራቸውን ምስክርነት ሰጥተዋል።
የሆስፒታሉ ሠራተኞች ዶር ጸጋይ የጀመሩትን ራዕያቸውን ሥራ እውን ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን በዚሁ ወቅት ገልጸዋል::

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጠንካራ አመራሩን በማጣቱ ጥልቅ ሀዘኑን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመዶቻቸው፣ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
August 21, 2026 4.4K 4