" ዜጎች ከማያውቁት ሰው ጋር በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ምንም ዓይነት ግንኙነት ባለመፍጠር ከመሰል ወንጀሎች ራሱን ሊጠብቅ ይገባል " - ፖሊስ
የተለያዩ ሴቶችን ፎቶ ግራፍ ከቴሌግራምና ከቲክቶክ በማውረድ በከፈተው ሀሰተኛ አካውንት እለቃለሁ ብሎ በማስፈራራት ክብርን በማዋረድና የፆታ ግኑኝነት በመጠየቅ የተጠረጠረን ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ።
ሀምሌ 30 ቀን 20017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰአት ተኩል ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ብሔረ ፅጌ መናፈሻ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።
አንተን አየሁ ሞላ የተባለው ተጠርጣሪ ራሱ ባዘጋጀው ሰቦንቱ ኤጀንት ሰርቪስ የሚል ሀሰተኛ የቲክቶክ አካውንት በመክፈት የግለሰቦችን ፈቃደኝነት ሳይጠይቅ ከቴሌግራም፣ ከቲክቶክ እንዲሁም ሴቶችን መንገድ ላይ በሚጓዙበት ወቅት ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረፅ ራሱ በከፈተው አካውንት ላይ አቀናብሮ በመልቀቅ ግለሰቦችን በማስፈራራትና በማስገደድ የፆታ ግኑኝነት ጭምር የሚጠይቅ ግለሰብ መሆኑን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ተከሳሹ ወይዘሮ ሰላማዊት ታደሰን የቤት ተከራይ መስሎ በመቅረብ ስልክ ቁጥሯን በመውሰድ የራሱ ባልሆነ ስልክ ቁጥር በመጠቀም ከቴሌግራም ላይ ፎቶዋን በማውረድና በማቀናበር ግላዊ የፆታ ግኑኝነት ከሷ ጋር እንድትፈፀም ያቀናበረውን ሰነድ በማስፈራሪያነት በመጠቀም ያስገድዳታል።
የግል ተበዳይም " ባለትዳርና የልጆች እናት ነኝ ይህንን ድርጊት ለመፈፀም ፈቃደኛ አይደለሁም " ብትለውም ማስፈራራቱን ባለማቋረጥ ባዘጋጀው ሀሰተኛ የቲክቶክ አካውንት " ሹገር ማሚ " ስለሆነች በእኔ አካውንት ማግኘት ትችላላችሁ በማለት ከአንድ ሺ በላይ ተከታይ ባለው የቲክቶክ አካውንት በማጋራቱ የግል ተበዳይ ለፖሊስ አመልክታለች፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሴቶች እና ህፃናት ወንጀሎች ምርመራ መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
በተጠርጣሪው ግለሰብ ላይ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ተግባር ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈፀም ካዘጋጃቸው ፎቶዎች ጋር መያዙንም ፖሊስ አስታውሷል፡፡
ዜጎች ከማያውቁት ሰው ጋር በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ምንም ዓይነት ግንኙነት ባለመፍጠር ከመሰል ወንጀሎች ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
Forwarded fromTIKVAH-ETHIOPIA
1
1August 20, 2025 482 3



