#Update
የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል !
በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የጭካኔ የግድያ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎች ጥፋተኞች ተብለው የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው።
ተከሳሾቹ ለፍርድ ውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል በማለት " የቆየ ህመም አለብን " ቢሉም የመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሃኪሞች የምርመራ ማስረጃ " የቆየ ህመም የለባቸውም " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የመቐለ ማእላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ ግድያ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?
የተጠርጣሪ ጠበቆች ትናንት ሀምሌ 3 " ደምበኞቻችን የቆየ ህመም አለባቸው ይህንን ለማረጋገጥ የህክምና ማስረጃ ለአርብ ሀምሌ 4 እናቀርባለን " ብለው ነበር።
ፍርድ ቤቱ ይህን ተቀብሎ ለዛሬ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ዛሬ አርብ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም ከመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰዓት በፊት ቤተሰብ የሚገኙባቸው የሚድያና የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎች በፍርድ ቤቱ በራፍ ደርሰው ተሰባስበዋል።
ተከሳሾች ለውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል ብለው የጠየቁት የህክምና ማስረጃ የቆየ ህመም እንደሌለባቸው አረጋግጧል።
ዳኞችም ይህን ካረጋገጡ በኋላ በተከሳሾች ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል።
አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ያሬድ ገብረስላሰ በላይ እና ኣንገሶም ሃይለማርያም በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመርካታቸው የገለፁት አስተያየት ሰጪዎች የወንጀል ደርጊቱን ከማጠራት እስከ ምርመራና ውሳኔ ድረስ በችግሮች የተተበተበ እንደነበር በመግለፅ ማረሚያ ቤት የፍርድ ውሳኔውን በጥብቅ እንዲተገብረው ጠይቀዋል።
" የጭካኔ ግድያው የሞት ፍርድ ያሰጥ ነበር " ያሉ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የተበዳይ ቤተሰቦች ወደ ቀጣዩ የፍርድ ቤት ይግባኝ ይጠይቁ " ብለዋል።
ከነሀሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም የተጓዘው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ በዚሁ ተቋጭቷል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን ልኳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ የእንስቷን ግድያ ከመነሻው እስከ ፍርድ ሂደቱ ሲከታተል ቆይቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
Forwarded fromTIKVAH-ETHIOPIA
July 11, 2025 10.8K 1



