#Update
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ቀጠሮ ሰጠ።
ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በእስር የሚገኙ ተከሳሽ ተጠርጣሪዎች ለውሳኔ ማቅለያ የሚሆን የህክምና ማስረጃ እናቀርባለን ባሉት መሰረት ለዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ዛሬ ችሎት ላይ የቀረቡት የተከሳሽ ጠበቆች " የመቐለ ዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ አርብ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የህክምና ማስረጃ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶናል " ብለዋል።
ፍርድ ቤቱም ይህን አድምጦና ተቀብሎ የመጨረሻ ቀነ ቀጠሮ ለነገ ሰጥቷል።
በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት የተበዳይና ተከሳሽ ቤተሰቦች ፣ በርካታ ሚድያዎች ፣ በሴት ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ስቪክ ማህበራት አመራሮችና አባላት ተገኝተው ነበር ።
ሁለት አመት ያስቆጠረው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ነገ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ መቋጫ የፍርድ ውሳኔ ያገኝ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የችሎቱን ውሳኔ ተከታትሎ ያቀርባል።
ቲክቫህ ኢትጵዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
Forwarded fromTIKVAH-ETHIOPIA
July 11, 2025 8.3K 1

