የገዛ የ12 ዓመት እህቱን የደፈረው ተከሳሽ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ! በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ የ12… — Setaweet (ሴታዊት) — TG.ME

Forwarded fromTITIKVAH-MAGAZINE
የገዛ የ12 ዓመት እህቱን የደፈረው ተከሳሽ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ!

በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ የ12 ዓመት ታናሽ እህቱን የደፈረው ተከሳሽ በዛሬው ዕለት በችሎት ቀርቦ ጥፋተኛ ተብሏል።

ተከሳሹ ድርጊቱን ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እህቱን በማታለል ወደ ጫካ ከወሰደ በኋላ መፈጸሙን የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሹ በዐቃቤ ህግ ድርጊቱን ስለመፈጸሙ የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ መፈጸሙን በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል በዝርዝር አምኗል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የቁጫ ወረዳ ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

መረጃው የቁጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@TikvahethMagazine
July 10, 2025 31.6K