ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ ዩቲዩብ አዲስ ይዘት የሚፈጥሩ አካላት… — 𝗦𝗔𝗠𝗜 𝗧𝗜𝗣𝗦📱 — TG.ME

AI Post Overview

YouTube удвоил пороги для входа в Partner Program: с 1 февраля 2027 года требуется 8000 часов просмотра длинных видео или 20 млн просмотров Shorts за 90 дней при сохранении 1000 подписчиков.

ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ

ዩቲዩብ አዲስ ይዘት የሚፈጥሩ አካላት ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም ገቢ ማግኘት የሚጀምሩበትን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ።

እ.ኤ.አ Feb 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፣ አዳዲስ ፈጣሪዎች በዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም ተቀብለው ገቢ ማግኘት ለመጀመር ፦

በመደበኛ/ ረጃጅም ቪዲዮዎች ላለፉት 12 ወራት 8,000 የታዩ ሰዓታት /Watch Hours/ ማሟላት አለባቸው። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው።

በአጭር ቪዲዮዎች /Shorts / በኩል ማመልከት የሚፈልጉ ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን የታዩ ዕይታዎች ማሳካት ይኖርባቸዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል።

የ1,000 ተከታዮች መስፈርት አልተለወጠም።

ይህ ለውጥ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ የአጭር ይዘት ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸውን ለማስቀጠል በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን እይታዎችን ጠብቀው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።

😳🙊
😱31❤21😢13😭8🕊4🤩3🤔1
August 11, 2026 23.7K 18 21