መሬታቸው ለሚኒሻ‼ ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ወገኖች መሬታቸው ለሚሊሻ ሊሰጥ ነው ተባለ‼ ​ከምስራቅ ወለጋ ኪራሙ… — ሪፖርተር ET — TG.ME

መሬታቸው ለሚኒሻ

ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ወገኖች መሬታቸው ለሚሊሻ ሊሰጥ ነው ተባለ

​ከምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ተፈናቅለው በወሎ ጃራ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች፣ ወደ ቀደመ ይዞታቸው በአካል ተመልሰው ካልገቡ መሬታቸው ለሚሊሻ፣ ለጸጥታ ኃይሎችና ለሥራ አጥ ወጣቶች እንደሚታደል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።

​ተፈናቃዮቹ መሬታቸውን ላለማጣት ሲሉ ከመጠለያ ጣቢያ ሆነው የተከማቸና ዓመታዊ ከፍተኛ ግብር እየከፈሉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ይህ አዲስ መመሪያ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና እንደፈጠረባቸውና መንግሥት ጣልቃ ገብቶ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

​በጉዳዩ ላይ በአካባቢው አመራሮች መካከል የሃሳብ ክፍፍል መኖሩ የተገለጠ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ "ግብር እየከፈሉ በመሆኑ ይዞታቸው ሊነካ አይገባም" ሲሉ፣ የቀሩት ደግሞ "በአካል በቦታው የሌሉ በመሆኑ መሬቱ መተላለፍ አለበት" የሚል አቋም ይዘዋል ሲል የዘገበው አዲስ ማለዳ ከአካባቢው የዞንና የወረዳ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም ብሏል።
❤8
June 24, 2026 4.3K 1