የቴዲ አፍሮ የቀድሞው ማናጀር አቶ አዲስ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የጃኖ ባንድ መስራች የነበሩት እና የሙዚቀኛ ገሰሰ ዘለቀ ወንድም የሆኑት ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲዮሰርና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ በአሜሪካን ሀገር ህይወታቸው ማለፉን የቅርብ ወዳጆቻቸው አስታወቁ።
አቶ አዲስ ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፉትን የቦብ ማርሊ ልጆችንእና በርከት ያሉ ታዋቂ ሙዚቀኞችን የማማከርና የማስተዳደር ስራ የሰሩ ጉምቱ የሙዚቃ አስተዳደር ባለሞያ ነበሩ።
አቶ አዲስ የቴዲ አፍሮ ማኔጀር በመሆንም ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።
በትላንትናው እለት አመሻሹ ላይ በኒው ጀርሲ ግዛት ህይወታቸው ያለፈው አቶ አዲስ ገሰሰ፤ የሞታቸው ምክንያት ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን አስከሬናቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ እንደታሰበ ተነግሯል።

4June 19, 2026 4.3K 1