ህውሃት በራያ አላማጣ ‼ የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ወሎ አቅጣጫ በእግር እንዲንቀሳቀሱ መታዘዛቸው ተገለጠ‼… — ሪፖርተር ET — TG.ME

ህውሃት በራያ አላማጣ

የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ወሎ አቅጣጫ በእግር እንዲንቀሳቀሱ መታዘዛቸው ተገለጠ

የህወሃት ታጣቂዎች በአላማጣ በኩል ወደ ወሎ መስመር በእግር ጉዞ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መተላለፉ ተሰማ። ስለሁኔታው የደረሱኝ መረጃዎች :-

📌 ታጣቂዎቹ ጉዟቸውን ያደረጉት ወደ ወልቃይት መስመር ሳይሆን ወደ ወሎ አካባቢ ሲሆን፣ ይህም ግጭቱን በወሎ መስመር ላይ ለማተኮር የተደረገ እቅድ እንደሆነ ተጠቁሟል።

📌 በተሽከርካሪ መጓዝ የሚያስከትለውን ከፍተኛ አደጋ ለመቀነስና ለጥንቃቄ ሲባል ታጣቂዎቹ በእግር እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል።

📌 በተለይ «አርሚ 15» የተባለው የጦር ክፍል በእግር ጉዞውን እንዲያከናውንና በመቀጠልም ወደ ኤርትራ አቅጣጫ እንዲያቀና መመሪያ እንደተሰጠው ተገልጿል።

📌አሜሪካ ዛሬ በሰሜን ኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው ቀጠና ያለውን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥለዋል ባሏቸው የህወሓት አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ገደብ መጣሏ ይታወሳል።

ቴሌግራም ቻናላችንን JOIN በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በትኩሱ ይከታተሉ 👇
  ■➥   http://T.ME/REPORTERETH
  ■➥   http://T.ME/REPORTERETH
❤5👍2😁1
June 19, 2026 4.1K 3