አንዲት ሴት አለች… እራሷን እየጠበቀች ለማይገባት ሰው ልትዳር የምትታጭ። አንዲት ሴት አለች ከማግባት የበለጠ… — Pp of Pp ꨄ — TG.ME

Pp of Pp ꨄአንድ ወንድ አለ ከስሜቱ ጋር እየታገለ የሚኖር፣ ትዳር ፈልጎ ትዳር የተወደደበት። አንድ ወንድ አለ የሚረዳው ያላገኘ፣ ልፋ ብቻ የሚል ፍርድ የተፈረደበት። አንድ ወንድ አለ ልቡ ተሰብሮ ምንም እንዳልሆነ ጠንክሮ የሚንቀሳቀስ። አንድ ወንድ አለ ከዘመድ መጠጋት፣ ከሰው መቀላቀል የሚያስፈራው፣ እራሱን ለሁሉም ኃላፊነት በታትኖ ለራሱ መሆን ያቃተው። አንድ ወንድ አለ እናት እና ሚስት መሆን የምትችል ሴት የሚፈልግ፣…
አንዲት ሴት አለች… እራሷን እየጠበቀች ለማይገባት ሰው ልትዳር የምትታጭ። አንዲት ሴት አለች ከማግባት የበለጠ ሊያገቧት የፈለጓት የሚያስፈራት። አንዲት ሴት አለች ብን ብላ ከቤተሰቦቿ መለየት ፈልጋ ሀያዕ ይዟት የተቀመጠች። አንዲት ሴት አለች በልጅነቷ ጥቃት ደርሶባት ለማንም ትንፍሽ ሳትል ኖራ በቤተሰብ በኩል ትዳር ሲመጣላት የምትበረግግ። አንዲት ሴት አለች ከገላዋ በቀር ምንም መስጠት የማትችልበት ሁኔታ ላይ ያለች። አንዲት ሴት አለች ልጅ አምሯታል፣ እናት መሆንን አጥብቃ ትፈልጋለች ግና ለልጇ አባት ለሷ ባል የሚሆናትን ትክክለኛው ሰው እስከሚመጣ ድረስ ስለምትጠብቅ የሆነ የደበቀችው ነውር አለባት ተብላ የምትታማ
💔15❤1🤝1
July 30, 2026 890 2