አንድ ወንድ አለ ከስሜቱ ጋር እየታገለ የሚኖር፣ ትዳር ፈልጎ ትዳር የተወደደበት። አንድ ወንድ አለ የሚረዳው ያላገኘ፣ ልፋ ብቻ የሚል ፍርድ የተፈረደበት። አንድ ወንድ አለ ልቡ ተሰብሮ ምንም እንዳልሆነ ጠንክሮ የሚንቀሳቀስ። አንድ ወንድ አለ ከዘመድ መጠጋት፣ ከሰው መቀላቀል የሚያስፈራው፣ እራሱን ለሁሉም ኃላፊነት በታትኖ ለራሱ መሆን ያቃተው። አንድ ወንድ አለ እናት እና ሚስት መሆን የምትችል ሴት የሚፈልግ፣ የልጆቹን እናት በጥንቃቄ የሚመርጥ። አንድ ወንድ አለ የሚወደውን ሰው ክብር ስለሚጠብቅ ሞኝ የተሰኘ፣ ድንበር አልፎ ስለማይባልግ ፈሪ የተባለ። አንድ ወንድ አለ ጉዳዮቹን ለራሱ መስጥሮ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈፀም ደፋ ቀና የሚል። አንድ ወንድ አለ ኃላፊነቶቹ ያጎበጡት፣ የሚንከባከባቸው ነፍሶች በዝተው የራሱን ነፍስ የረሳ አንድ ወንድ አለ።
.
..
7
6
1July 30, 2026 834 2