🔬 ስለ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማዕከላዊ ቤተ-ሙከራ ምን ያህል ያውቃሉ?
ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም
+++++++++++++++++++++++++++
የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ማዕከላዊ ቤተ-ሙከራ ጥናታዊ ምርምሮችን ወደ ተጨባጭ ውጤት፣ ሃሳቦችን ወደ ታላቅ ፈጠራ፣ እንዲሁም ሳይንሳዊ ትንተናዎችን ወደ እውነተኛ ዓለም መፍትሄዎች የሚለውጡበት ማዕከል ነው።
ማዕከሉ ለተመራማሪዎች፣ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለኢንዱስትሪዎች፣ እንዲሁም ለመንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ዘመናዊ እና የተሟሉ የቤተ-ሙከራ (ላቦራቶሪ) ቁሳቁሶችን ከብቁ ባለሙያዎች ጋር አዘጋጅቶ ይጠብቀዎታል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች የላቀ ድጋፍ የሚያደርጉ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ያሟላ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፡
•ከፍተኛ አቅም ያላቸው የግንባታ ግብዓትና የሃይድሮሊክ ሙከራዎች
•የቁሳቁስ (Materials) ጥናት ሙከራዎችን
•የስነ-ምግብ እና የስነ-ህይወታዊ (Food and Biological) ትንተና
•የኃይል እና አካባቢ (Energy & Environment) ምርምር
•የማዕድናትን እና ስነ-ምድር (Minerals and Geology) ጥናት ዘርፎች
•እና ሌሎች በርካታ ዘመናዊ የቤተ-ሙከራ አገልግሎቶች ይገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ
📞 ስልክ ቁጥር: +251 993 807 178
ጥራትን፣ ብቃትን እና ፈጣን አገልግሎትን ከባለሙያዎቻችን ጋር ያግኙ!
August 19, 2026 6.5K 7









