ዕድሜ ለእርሶ ከጠፈረን እግር ተወርች -ካነቀፈን የዘር ደቦ፡ በየጥሻ ካስመሸገን -በመንደሩ ተተብትቦ፡ “ሰዉ… — መጽሐፍቶችን በpdf📚 — TG.ME

ዕድሜ ለእርሶ

ከጠፈረን እግር ተወርች -ካነቀፈን የዘር ደቦ፡
በየጥሻ ካስመሸገን -በመንደሩ ተተብትቦ፡
“ሰዉ “መሆን ነዉ መሻገሪያ የሚያስታርቅ ከሀያሉ፡
ሲወተዉት ልስልስ ድምፆ - ሳይሰምርልን ህያዉ ቃሉ ፡
አለቅሳለሁ በመደቤ -እንቅልፍ የለኝም እንዳሉ፡
ሄዱ አሉ ?

ላንቀላፋነዉ እኛ -ዓለም ዘመን እያለፈን ፡
እሺ ብንል ምን ነበረ ? መካሪ አባት ሳያኮርፈን ፡
ሄዱ አሉ ?

አሜን ሳንል እጅ ስመን ፡
ሳንታረቅ ከእልህ ከስመን ፡
እልፍ ሳንል ጋት እርምጃ፡
ሳይሞላልን ስለት ሀጃ ፡
እንኳንስ ከደም ዕዳ ፡
ሳናወጣ ብድር ቀዳ ፡
አባት ሄደ የእልፍኝ ማገር ፡
ስመ መልካም ልበ ገር ።
እንዲህም የለ መሰበር !!

ፍትህ ሞተ ፣እዉነት ሞተ ፣አባት ሞተ ሲለን ጀማዉ ፡
የማጣት ብርድ ፣ ያዘን ቆፈን ፣ አጥንት ስር የሚሰማዉ ።
አግኝቶናል ባደባባይ ፣ ከመለስዎ የዕንባ ጎርፉ:
ባልታዘዝንዎ ይቅር በሉን _በዲናችን በሉን አፉ ።

ዕድሜ ለርሶ

“ዕድሜ ለርሶ “ ለሞተ ሰዉ አይባልም እንዳይሉ ፡
መጥኔዉ ለኛ ዕድሜዉ ለርሶ ተለዉጧል ብሂሉ፡
የዕምነት ትርጉም እንደዚህ ነዉ ዘር ተሻግሮ ኬላ ጥሶ፡
መከበርን አየንበት አወቅንበት ዕድሜ ለእርሶ ፣፣

በመኖርዎ የዘሩትን _በመምትዎ ደግመዉ ካሱን
የረሳነዉ የተዉነዉን “ሰዉነትን “ አስታወሱን
በጭንቃችን ተደርበዉ _እንደገና ሆድ አስባሱን ።

ሄዱ አሉ?
በህይወት የተገለጠ -ፍቅር ፍትህን አንግሶ
መኖርስ በልብ ላይ -መሄድስ ልክ እንደርሶ ።

ነፍሶን ይማር የተከበሩ አባታችን።

“የሐገር🇪🇹መልክ”

መልካም በዓል🤙
❤12👌1
August 25, 2026 2.1K 3