📖 4One | ክርስቶስ እውነተኛ ሰው መሆኑን የሚክድ አስተምህሮ፣ የድነታችንን መሠረት የሚያናጋ ከባድ የእምነት ክህደት ነው!
ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን አልነሣም የሚል አስተምህሮ ትንሽ የትርጓሜ ልዩነት አይደለም፤ የሥጋ መልበሱን እውነት፣ የሰው ልጅ መሆኑንና የድነታችንን መሠረት የሚያናጋ ክህደት ነው።
ክርስቶስ የሰውነትን መልክ ብቻ የያዘ አምላክ አይደለም፤ እውነተኛ ሰው ሆኗል! ከቅድስት ከድንግል ማርያም ሥጋን ነሥቶ፣ እኛ ያለንን ሰውነት ተካፍሎ፣ ከኃጢአት ነጻ ሆኖ፣ እውነተኛ ሰውነትን ተዋሕዶ ተወልዷል።
« ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።»
(ዮሐንስ 1፥14)
« ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ፣ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው፤» (ዕብራውያን 2፥14)
ይህንን የእምነት አምድ በተአምራት፣ በድንቅ፣ በፈውስ፣ በትንቢትና በሚያስደንቁ ክንውኖች መሸፈን አይቻልም። ተአምር የአስተምህሮ ስሕተትን አያነጻም፤ የሰው ድንቅ ክንውንም የእውነት መለኪያ አይሆንም!
ወንድሞችና እህቶች ሆይ፣ በሰው ዝና፣ በስሜታዊ ክንውንና በሚታዩ ድንቆች አትማረኩ። የምትከተሉትን አስተምህሮና አስተማሪ ፈትሹ። የሚሰብከው ቃል ከወንጌል ጋር ይስማማልን? የሚያውጀው ክርስቶስ የመጽሐፍ ቅዱሱ ክርስቶስ ነውን?
የክርስትናችን መሠረት የሰው ተአምር አድራጊነት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስና የወንጌሉ እውነት ነው!
«ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።»
(1 ዮሐንስ 4፥1)
ክርስቶስን በትክክል እናውቅ፤ ወንጌሉን ከማንኛውም የሰው አስተምህሮ በላይ እናክብር፤ ስሕተትንም በእውነት እንጋፈጥ!
4One | One Lord. One Faith. One Mission.
https://t.me/one_died_for_all
4 one
@one_died_for_all · 772 subscribers
that one died for all,
Information
Username@one_died_for_all
Channel history
We have been tracking it since August 18, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
These numbers aren’t from todayLast measured on September 28, 2026. The source has been silent since, so this is the last thing we saw — not the channel’s current state.
⌘K
Newest first
Share channel “4 one”
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/one_died_for_allIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →