ማደሪያ ክፍሌ ውስጥ በየት በኩል እንደምትገባ ያልገባኝ ግን ደግሞ ሁሌ ማታ ማታ ስትንኮሻኮሽ የማገኛት አንድ… — NK's Journal — TG.ME

ማደሪያ ክፍሌ ውስጥ በየት በኩል እንደምትገባ ያልገባኝ ግን ደግሞ ሁሌ ማታ ማታ ስትንኮሻኮሽ የማገኛት አንድ አይጥ አለች።

...ልክ መብራት አጥፍቼ ምናምን ልተኛ ስል ወደ missionኗ ትገባለች። ..

ከዚያ እሷን ለማስፈራራት የሆነ ወረቀት ነገር ሹክሹክ አደርጋለሁ።..

እሱን ስትሰማ .."ይኼ ብሽቅ ምንድነው የሚረብሸኝ?".. የምትል ይመስለኛል ደምጿን አጥፍታ ዝም ትላለች። ከዚያ እኔም ፀጥ ስል እሷ በተራዋ ማንኮሻኮሽ ትጀምራለች።

..ያዙት እንግዲህ እልህም ትያያዛለች እናንተ..

እና ምን እንደምትቆረጥም አላቅም ሁሌ ክፍሉን ሩዋንዳ ነው የምታደርገው።

ደግሞኮ Roommateኤ በሏት። አናወራም እንጂ እንግባባለን።

እሷ ምን እንደምትፈልግ እኔ አውቃለሁ። እኔ ምን እንደምፈልግ(መግደል) እሷም ሳልነግራት ታውቃለች።

አንዳንዴ አባሮሽ ስንጫወት እናመሻለን። በልጅነቴ መች ተጫወትኩ።

ጦሽ ሲያረጋት ደረቷን ነፍታ ትመጣና ... "ና እስኪ ንካኝ".. ማለቷ ነው መሠለኝ ገላምጣ ታልፋለች። ይሁን ብዬ ignore ሳደርጋት እንደገና ትመጣና ሞራሌን የሚነካ ነገር አድርጋ ሮጣ ትሄዳለች። እኔ ገብቶኛል ና አጫውተኝ ማለቷ ነው።

አንዳንዴ ከስራ ደክሞኝ እንደምገባ አይገባትም መሰለኝ። ይኼን እንኳን መረዳት ያቅታታል። እምቧ ከረዩ ትላለች ካላጫወትኳት። ሲጀመር ፆታዋ ሴት እንደሆነም ያወኩት በዚህ ድርቅናዋ ነው🙂። የሆነ ችክ ምትለው ነገር አላት።

አሁን ምን ይሉታል ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ፌስታል ማንሾካሾክ?

ብቻ ተዉ በሷ የተነሳ ብዙ የፍቅር ታሪኮችን እየተማርኩ ነው። እሷ ግን ክፉ ናት።

ሌላ አዲስ ነገር ካለ ተከታትዬ አሳውቃችኋለሁ።

ደህና እደሩ!

#reposted!

@NKs_Journal
😁25🤣4❤1🥰1
August 18, 2026 759 3 3