የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና ምዝገባ
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን የመግቢያ ፈተና በኦንላይን በመስጠት ለ2019 ዓ.ም መቀበል ይፈልጋሉ፡፡
የትምህርች ዘርፎች
በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች
ለትምህርት መስኮች ዝርዝር 👇
https://www.facebook.com/share/p/19EMVmakWg/ or
https://www.facebook.com/share/p/18zZo4rxUj/
የምዝገባ ጊዜ
ከነሐሴ 25 እስከ ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ
የምዝገባ ቦታ
የምዝገባ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በኦንላይን https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et / www.astu.edu.et በመጠቀም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን የምዝገባው ጊዜ ካበቃ በኋላ ይገለጻል ተብሏል።
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ
በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ።
በቂ አመላካቾች የሌሉባቸው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
🔔 አመልካቾች የመግቢያ ፈተና በሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች ማለትም (ከ9-12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብ እና እንግሊዝኛ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ ዩኒቨርሲቲዎቹ መክረዋል።
አመልካቾች ለፈተና ስትቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት፣ የፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር 💠
🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister

20
1August 30, 2026 6.5K 24