Info: post #4332 — TG.ME

" ' አታሼ' የሚለው የሥራ መደብ የጀማሪ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ባለሙያ የመነሻ የሥራ ደረጃ መጠሪያ ነው " - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

👉 " ማመልከቻ ሊንኩ ተስተካክሏል"

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ "በአታሼ (Attaché" በተሰኘ የሥራ መደብ 100 አመልካቾችን ለመቅጠር የሥራ ማስታወቂያ ማውጣቱን ይታወቃል።

ይህን ማስታወቂያ ተከትሎ በርካቶች ለመሆኑ "አታሼ" (Attaché) ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄ ሲያነሱ እና ሲወዛገቡ ተስተውለዋል።

በሥራው ለመሰማራት ሙከራ ያደረጉ ወጣቶች ደግሞ የሥራ ማስታወቂያው መውጣቱን ተከትሎ የተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ "አይሰራም" የሚሉ አስተያየቶችን እያቀረቡ ናቸው።

ይህን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ስለ "አታሼ" ምንነት እና ስለመመዝገቢያ ሊንኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊን ማብራሪያ ጠይቋል።

እሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ምላሽ፣ " በኢፌዴሪ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ባለሙያዎች የሙያ መሰላል መሰረት 'አታሼ' የሚለው የሥራ መደብ የጀማሪ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ባለሙያ የመነሻ የሥራ ደረጃ መጠሪያ ነው " ብለዋል።

ይህ የመጀመሪያው የሥራ መጠሪያ መሆኑን ገልጸው፣ "ከዚያ በኋላ ሦስተኛ ፀሐፊ ይባላል፤ ሁለት፣ አንድ እያለ ይቀጥላል" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአመልካቾች መመዝገቢያ ሊንክ አይሰራም በሚል ለሚነሳው ቅሬታ ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ "የአይሲቲ ባለሙያዎች ቼክ እያደረጉ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህን ካሉን ከቆይታ በኋላ ደግሞ፣ "ሊንኩ ተስተካክሏል" ብለዋል።

በ"አታሼ" የሥራ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሙያዎች ምን ምን ይሰራሉ? ስንል የጠየቅናቸው አመራሩ በሰጡን ምላሽ፣ "የመጀመሪያ ደረጃ እንደመሆኑ ሥልጠና የሚሰጥበት የሥራ ላይ ልምምድ የሚደረግበትና አጠቃላይ ከሙያው ጋር ትውውቅ የሚያደርግበት ነው" የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

"አታሼ" የሥራ አይነት የባህል፣ የሚዲያ ግንኙነት፣ የንግድ ግንኙነት ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎች ያሉት ሲሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት በተመደቡበት የሥራ አይነት የውጭ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን ማከናወን፣ ሪፖርቶችን ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ይታመናል።

መመዝገቢያ https://forms.gle/R7PmwCNeqEE3EQBN6 (በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪና 0 ዓመት የስራ ልምድ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
❤21👍4
September 3, 2026 5.8K 202