🔖 ማስታወቂያ
ለቁርአን ሒፍዝ ፈላጊዎች
በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር የሚገኘው የዳሩል ሒጅረተይን (ደረቶ) ቅርንጫፍ የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከል ለ2019/1448ሒ የሒፍዝ አዳሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለ2 ዓመት ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ብቻ በአካል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
▪️ፆታ፡ ወንድ
▪️የጤና ሁኔታ፡- ከተላላፊ በሽታ ነጻ የሆነ ጤነኛ
▪️ስነ-ምግባሩ ጥሩ የሆነ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
▪️ እድሜው ከ13 እስከ 20 የሆነ
የመርከዙን ህግጋት አክብሮ መማር የሚችልና አላማ ያለው በመርከዙ የተቀመጠውን የወጪ መጋራት የሚችል የተማረውን ለማህበረሰብ ለማስተማር ዝግጁ የሆነ
▪️የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል
🖍 ማሳሰቢያ
- ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ ከወላጅ ወይም ወኪል ጋር መምጣት አለባቸው።
- የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው መስከረም 13-12-2018 አ.ል ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ሲሆን ቦታውን ለምዝገባ ስትመጡ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ለምዝገባ ስትመጡ የወላጅ/ወኪል ፎቶ (የተማሪ እና የወላጅ) እና መታወቂያ ኮፒ እንዳይረሡ።
- የምዝገባ ቦታ፡ መርከዝ ኢብኑ መስዑድ18 (አዲስ አበባ) ስልክ 0911 591442 / 0950 122611
ቴሌግራም፡ @webaje1
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር









