ዛሬ ልባችንን ወደ አገራችንና ወደ ሕዝባችን እናድርግ።
በተለይም በሰሜን ላለው ሁኔታ ሰላምን፣ ለተጎዱት ፈውስና ምሕረትን፣ በድርቅና በራብ ላሉት ደግሞ አምላካዊ እርዳታና አቅርቦትን እንለምን።
ዛሬ ስለ ራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ሕዝባችን በእግዚአብሔር ፊት እንቁም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1-2
“እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።”
🙏 የጸሎት ነጥቦች
በአገራችን ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን እንጸልይ።
በተለይም በሰሜን ላሉት ሰዎች ሰላምና ጥበቃ እንዲሆን።
በግጭት የተጎዱትንና ቤታቸውን ያጡትን እግዚአብሔር እንዲያስብ።
በድርቅና በራብ የተጎዱ ቤተሰቦችን እግዚአብሔር እንዲያስብ።
ምግብ፣ ውኃና አስፈላጊውን አቅርቦት እንዲያገኙ እንጸልይ።
ለአገራችን መሪዎች ጥበብና የሰላምን ልብ እንዲሰጥ እግዚአብሔርን እንለምነው።
ተባረኩ፣ ፀጋ ይብዛላችሁ፣በርቱ🥰
#Prayer_week
#5KECSF
#Return
#Walk_righteously
#Trust
#SEEKING_GOD
Follow us on our digital platforms
TELEGRAM|INSTAGRAM|TIKTOK|YOUTUBE







