ተቀናሽ የሚደረጉ የሰራተኞች መስተንግዶና የማረፊያ ወጪዎች
ለድርጅትዎ የግብር ተቀናሽ የሚደረጉ የምግብ፣ የመጠጥ እና የመኖሪያ ወጪዎችን ደንብ ባጭሩ ይመልከቱ
1.የምግብ እና መጠጥ ወጪ ገደብ
የማዕድን፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የግብርና እና ሆርቲካልቸር ዘርፍ
ሰራተኞች በነጻ ለሚቀርብላቸው ምግብና መጠጥ የሚወጣው ወጪ ተቀናሽ የሚደረገው ከወሩ አጠቃላይ ደሞዝ እስከ 30% ብቻ ነው።
ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና የምግብ አገልግሎት ሰጪዎች
ለሰራተኞቻቸው የሚያቀርቡት የምግብና መጠጥ ወጪ ተቀናሽ የሚደረገው ከወሩ አጠቃላይ ደሞዝ እስከ 20% ብቻ ነው።
ማሳሰቢያ: ተቀናሽ የሚደረገው አልኮል የሌላቸው መጠጦች ወጪ ብቻ ነው!
2.የህጋዊ ማስረጃ መስፈርቶች
በራሳቸው አዘጋጅተው የሚያቀርቡ ከሆነ: የግብዓት ወጪዎቹ በህጋዊ ደረሰኝ ወይም የግዢ ማስረጃ መደገፍ አለባቸው።
በ3ኛ ወገን (አቅራቢ) የሚቀርብ ከሆነ:
የአቅርቦት ውል
አገልግሎቱ መገኘቱን የሚያሳይ የድርጅቱ ማረጋገጫ
የክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ
3. የማረፊያ ቤት ወጪ (ከከተማ ርቀው ለሚሰሩ)
በማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ ወይም ግብርና ዘርፍ የተሰማራ ድርጅት ከከተማ ርቆ ለተመደበ ሰራተኛ በነጻ የሚያቀርበው የማረፊያ ቤት ወጪ ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ ይደረጋል!
"ከከተማ ርቆ የሚገኝ ቦታ" ማለት ምን ማለት ነው? ቢያንስ 20,000 ነዋሪ ካለው ከተማ ወሰን 30 ኪሎሜትር እና ከዚያ በላይ ርቆ የሚገኝ ቦታ ነው።
ግብር÷ ለሃገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.yout

15
2August 14, 2026 8K 3 71