የኦዲት አሰራር ግልጽነትን ለማሳደግ ያለመ የስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ
****************************************************************
(ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመካከለኛ ግብ ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
በስጋት መስፈርት ደረጃ ተመርጠው ኦዲት ለሚደረጉ ድርጅቶች የታክስ ህግ ተገዥነትን ለማሳደግ፣ የኦዲት ሂደቱን ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲሁም የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠናዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ ላይ የመነሻ ሰነድ ያቀረቡት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል እንደገለጹት፤ የኦዲት አሰራር ዋና ዓላማ ግብር ከፋዮች ህግን ጠብቀው እንዲሰሩ ለማስቻልና ክፍተቶችን በጋራ ለማረም እንጂ ጫና ለመፍጠር አይደለም ያሉ ሲሆን፤ በመነሻ ሰነዱ የኦዲት አሰራር ስርዓት እና ደረጃዎች፣ኦዲት የሚከናወንበት ግልጽ አሰራር፣ ቅድመ-ኦዲት ዝግጅት ፣ድርጅቶች ኦዲት ከመጀመሩ በፊት ማድረግ የሚገቧቸው ቅድመ ዝግጅቶች፣ መቅረብ የሚገባቸው ሰነዶች ፣የደረሰኝ ህጋዊነት እና ተያያዥ ማስረጃዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረብ ያለባቸው ሰለመሆኑ ፣የኦዲት ግኝት (Audit Findings) እና ምላሽ፡ በኦዲት ሂደት የሚወጡ ግኝቶች ለግብር ከፋዩ የሚገለጽበትና ድርጅቶችም የራሳቸውን ማብራሪያና ማስረጃ የሚያቀርቡበት ህጋዊ አሰራር የሚሉት በቀረበው ሰነድ በስፋት ከተዳሰሱ ነጥቦች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የውይይት መድረኩን በጋራ የመሩት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል እና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ በላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
በተለይም ከተሳታፊዎች ከኦዲት ግኝቶች አወሳሰን፣ ከሰነድ አቀራረብ፣ ከውሳኔ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፤ ከአመራሮቹ ለአሰራር ግልጽነት ቅድሚያ እንደሚሰጥና የሚነሱ ክፍተቶች በመሙላት ለግብር ከፋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ በትኩረት እየተሰራ ያለ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጻል።
በመጨረሻም ወ/ሮ ሮዛ ጀማል ባቀረቡት የማጠቃለያ ሀሳብ፤ ግብር ከፋዮች አስፈላጊውን ሰነድ በወቅቱ በማቅረብና ግልጽ አሰራርን በመከተል ለኦዲት ስራው ስኬት ተባባሪ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ግብር÷ ለሃገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል ላይ እንገኛለን
Telegram
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2
This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2.
Join the channel.

5
1September 1, 2026 2.4K 6