ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብርን ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ለግብር ከፋዩ የታክስ እወቀት እያስጨበጠ ይገኛል… — M.O.R East Addis Ababa Branch — TG.ME

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብርን ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ለግብር ከፋዩ የታክስ እወቀት እያስጨበጠ ይገኛል
...........................
ሀምሌ 8 /2018 የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አዳዲስ ግብር ከፋዮችን መሰረታዊ የታክስ ህጉን እንዲረዱ በማድረግ ካላስፈላጊ ቅጣት ማዳን ፣ግብርን በመክፈል ሀገራዊ ሀላፊነትን እንዲወጡ ማሰቻል ዓላማ አድርጎ ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች መሀከል ለአዳዲስ ግብር ከፋዮችን የሚሰጠው የግንዛቤ ስልጠና አንዱ ነው ፡፡ በዛሬውም እለት በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች የግማሽ ቀን የማስጨበጫ ስልጠና ሠጥቷል፡፡
አቶ አቶ ውቡ ፋንታው የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ ስልጠናውን የሰጡት ሲሆኑ በስልጠናው ላይም በቅድመ ግብር ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ዙርያ ላይ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ አቶ አዲሱ ኡርጌሳ የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ስነምግባር ከፍተኛ በለሙያ በስልጠናው ላይ ተገኝተው የንግድ ስራ የተቀላጠፈና ጤናማ እንዲሆን በሚያስችል ዙርያ የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል፣በቅርንጫፍት/ቤቱ ግልጋሎት ላይ የሚገጥም ማናቸውም የስነምግባር ብልሹነት ቢገጥም የጥቆማ ስርዓትን በመጠቀም ማሳወቅ እንደሚገባና በአካልም በመቅረብ ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል::
❤7🙏1
August 14, 2026 4.3K 1