የታክስ ህጎች፣ ለግብር ከፋዮች በተከታታይ የሚሰጠውን “ሞጁላር” የተሰኘ ስልጠና መስጠቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል… — M.O.R East Addis Ababa Branch — TG.ME

የታክስ ህጎች፣ ለግብር ከፋዮች በተከታታይ የሚሰጠውን “ሞጁላር” የተሰኘ ስልጠና መስጠቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል
............

ነሀሴ 5/2018 //በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት //
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በታክስ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለግብር ከፋዮች በተከታታይ የሚሰጠውን “ሞጁላር” የተሰኘ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥላል ፤በዚህም የበጀት ዓመቱ የነሀሴ ወር የሞጁላር ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ የሺወርቅ ተጫነ የስልጠናውን መጀመር አስመልክተው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ታክስ ከፋዮች በቂ የታክስ ዕውቀት ኖሯቸው ግብራቸውን በሃላፊነት አዋጅ ፣ህግንና መመርያን ተከትለው መክፈል እንዲችሉ ታሰቦ ስለጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል ።አያይዘዉም ከሰልጣኞች የሚጠበቀው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ያገኙትን ስልጠና ተገባር ላይ እንዲውሉ አሳስበዋል፡፡
ከዚህ ጋር አያይዘው የሥራ ሂደት አስተባባሪዋ በእለቱ በክፍል ሁለት (ሁለተኛ ሴመስቴር ) እየተማሩ ያሉትን የሞጁላር ሰልጣኞችን የትምህረቱ ሂደት ምን እንደሚመስል ምልከታ በማደረግ ሰልጣኞች ተገቢውን ስልጠና እያገኙ መሆናቸውን ለማወቅ ችለዋል ፡፡
በመቀጠልም አቶ ውቡ ፈንታው የታክስ ከፋዮች ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ በመጀመሪያ ሴምስተር ከሚሰጠው ስልጠና መሀከል ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚለውን ርአስ ለሰልጣኞቹ ማሰልጠን ጀምረዋል፡፡
የሞጁላር ስልጠውን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሙያተኞች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት የሞጁላር ስልጠናውንም አየተከታተሉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡

………….



ትክክለኛውን የዩቲዩብ እና የፌስቡክ አድራሻችን ይወዳጁ፤ የታክስ ትምህርቶችና ልዩ ልዩ ታክሳዊ መረጃዎችን ይከታተሉ!!
M.O.R East Addis Ababa Branch
ቲክቶክ አካውነት https://vt.tiktok.com/ZSapr1yoT/
ቴሌ ግራም https//t.me/moreastaa
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCaS60GHxhnCrPTcIjsd6nbw
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Moreastaddisababa
Telegram (https://t.me/moreastaa
ለአስተያትዎ ሃሳብ መስጫ ቴሌግራም https://t.me/EastTaxPayersGroup
የእውቀት አድማስዎን በማሰፋት ግብርዎን በህግንና ደንብን መሰረት በማድረግ በጊዜው ለማሳወቅ፣ ለመክፈል እንዲችሉና ካላስፈላጊ ቅጣትና ወጪ ለመዳን በእውቀት የታገዘ ስራ ለመስራት የሞጁላር ስልጠናን ይመዝገቡ !!
የድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትት ስራ አስኪያጅ ከሆኑና ጊዜ ከሌለዎት የርቀት ትምህርት በመመዝገብ ይማሩ !
Telegram
M.O.R East Addis Ababa Branch
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
❤14
August 11, 2026 6.5K 4