በጧቱ የሰማሁት ልብ የሚያሞቅ ታሪክ ... አቡበከር ረዲየሏሁ አንሁ ሁሌ ሱብሂ ከሰገደ በኋላ ከመዲና ከተማ… — Mirjan Digital — TG.ME

☀️
በጧቱ የሰማሁት ልብ የሚያሞቅ ታሪክ ...

አቡበከር ረዲየሏሁ አንሁ ሁሌ ሱብሂ ከሰገደ በኋላ ከመዲና ከተማ ይወጣ ነበር ። ይሄንንም ድርጊቱን ኡመር ረዲየሏሁ በተደጋጋሚ ይመለከትና የት እንደሚሄድ ለማወቅ አንድ ቀን ሰግዶ ሲወጣ በድብቅ ይከተለው ጀመር ። ኡመር ሰውነቱ ፈርጠም ከማለቱ ጋር እንዳያየው በጥንቃቅ ይጓዝ ነበር ።

አቡበከርም ድንበር ላይ የምትገኝ መንደር ውስጥ ወዳለች ደሳሳ ቤት ገባ ። ኡመር ከቅርብ ርቀት ሁነው  እስኪወጣ ይጠባበቁት ነበር ። ነገር ግን አቡበከር ረዘም ያለ ሰአትን ቆይቶ ወጣ ። ኡመርም የአቡበከርን መውጣት ተከትሎ እሱ የገባበት ቤት ገባ ። በውስጧም አንዲት አይነስውር አሮጊት ሴት ያገኛል።

"አሰላሙ አለይኩም እዚህ ቤት " በማለት ገባ እርሷም መለሰችለት ።
"አሁን እዚህ ቤት ገብቶ የነበረው ሰው ምንሽ ነው " አላት
<<" ባሪያዬ ነው ">> አለች 
"ቀን በቀን ይመጣል ቤቴን አፅድቶ ፣ሊጥ  አብኩቶ ቂጣ ጋግሮልኝ ፣ ለቀን ውሎዬ የሚያስፈልገኝን ሰርቶልኝ ይሄዳል" አለች።
"ስንት ነው የምትከፍይው " አሏት
"ምንም አልከፍለውም ዱአ ብቻ ነው የማደርግለት" አለች

ኡመርም በመገረም ምንም ሳይናገሩ ከቤት ወጥተው
" ያ ኸሊፈተ ረሱሊላህ ! ለምንድነው ህይወታችንን እንዲህ የምታከብደው?" አለ
(በመልካም ስራ ይሽቀዳደሙ ስለነበር )  رضي الله عنهما وأرضاهما

አስባችሁታል ...
አለምን አስተዳዳሪ መሪ ፣ የነብዩ ምትክ
የአንዲት አሮጊት ሴት ባሪያ ነበር ።

መኩራራታችን ትተን ለአኺራ የሚጠቅመንን
ብንሰራ ነው የሚያዋጣን !


@keras_gar_weg
September 2, 2026 25