ዲግሪዬ ነርሲንግ ነው፤ ስራዬ ግን ዲዛይን!" 🏥🎨 ​ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች! ዛሬ ትንሽ ስለ ጉዞዬ… — Mirjan Digital — TG.ME

"ዲግሪዬ ነርሲንግ ነው፤ ስራዬ ግን ዲዛይን!" 🏥🎨
​ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች! ዛሬ ትንሽ ስለ ጉዞዬ ላውጋችሁ፦
🔹 2009፦ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ጅማሮ። ግን ብዙም ሳይቆይ ‘ላግ’ አድርጎ መመለስ።
🔹 2010-2013፦ በሪፍት ቫሊ የነርሲንግ ጥናት። ጎን ለጎን ደግሞ በስልኬ ግራፊክስ ዲዛይን መለማመድ።
🔹 2013-አሁን፦ በጤና ሙያ ተቀጥሮ መስራት።

​የክፍለ ሀገር ልጅ ሆኜ ለቴክኖሎጂ ያለኝ ፍቅር ከነርሲንግ ጋውን ጋር ተጋጭቶ ለዓመታት ግራ አጋብቶኝ ነበር። 'የኔ Career ምንድነው?' የሚለው ጥያቄ ሰላም ቢነሳኝም፣ በ2018 ዓ.ም ግን አንድ ወሳኝ እርምጃ መራመድ ጀመርኩ።

​ይህ ቻናል የዚህ ጉዞ ውጤት ነው። አብራችሁኝ ሁኑ! 🚀

👇👇👇
t.me/mirjan_digital
September 5, 2026 23 1