በMeta platforms(Facebook, Instagram) ላይ ማስታወቂያ ለመስራት ሁለት አይነት መንገዶች… — Mirjan Digital — TG.ME

Forwarded fromFEFewzan Tech®
በMeta platforms(Facebook, Instagram) ላይ ማስታወቂያ ለመስራት ሁለት አይነት መንገዶች አሉ።

Facebook Boostና Facebook Ads Campaign

የነዚህ ነገሮች ልዩነታቸውና ጥቅማቸው ምን እንደሆነ በዝርዝር ልንገራችሁ።

Facebook Boost
በፌስቡክ ፔጅ ላይ ቀድሞ የተለቀቀን post በቀላሉ ሰማያዊዋን "Boost Post" በተን በመጫን
ለብዙ ሰው በፍጥነት እንዲደርስ የምናስተዋውቅበት መንገድ ነው።

Pros (ጥቅሞች)፦
⚫Quick & Easy፦ ምንም ጥልቅ የዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀት አይጠይቅም። በደቂቃዎች
ውስጥ ማስተዋወቅ ትችላለህ።
⚫Beginners Friendly፦ ውስብስብ ነገሮች የሉበትም።
Engagement ለመጨመር አሪፍ ነው፦ ፖስትህ ብዙ Likes, Comments, እና Shares እንዲያገኝ ይረዳል።
⚫Low Budget፦ በትንሽ ብር መጀመር ይቻላል።

ጉዳቶች
⚫Targeting ውስን ነው፦ ማስታወቂያውን እንዲያይ የምንፈልገውን ሰው (Audience) በጥልቀት መምረጥ አአያስችልም።
⚫Detailed Objective ማስተካከል አይቻልም፦ የማስታወቂያው ዋና ዓላማ ሽያጭ ወይም Lead ማግኘት ቢሆን እንኳን Boost በአብዛኛው የሚያተኩረው Engagement (ላይክ እና ኮሜንት) ላይ ብቻ ነው።
⚫Placement መቆጣጠር አይቻልም፦ ማስታወቂያው በፌስቡክ feeds, Reels, story ወይም በInstagram ላይ ብቻ ይታይ የሚለውን ለመወሰን አያስችልም።

Facebook Ads Campaign
ይህ በMeta Ads Manager አማካኝነት የሚሰራ በጣም ፕሮፌሽናልና ስትራቴጂካዊ የሆነ የማስታወቂያ አሰራር መንገድ ነው።
ማስታወቂያውን ከባዶ (from scratch) ሁሉን ነገር በማስተካከል ለመስራት ያስችላል።

ነገር ግን ማስታወቂያው በኛ በራሳችን page ላይ አይለቀቅም። ይህም Dark Post ይባላል።

ጥቅሞች
⚫Advanced Targeting፦ ማስታወቂያህ በትክክል ለሚገዙህ ሰዎች ብቻ እንዲደርስ ማድረግ ያስችላል።
⚫Custom Audience
⚫የተለያዩ Campaign Objectives፦ ሽያጭ ለመጨመር (Sales)፣ ድረ-ገጽ ላይ ሰዎችን ለመውሰድ (Traffic)፣ መረጃ ለመሰብሰብ (Leads) ወይም ለመልእክት (Messages) የሚሆኑ ልዩ ልዩ ምርጫዎች አሉት።
⚫A/B Testingና ማሻሻል፦ የተለያዩ ምስሎችንና ፅሁፎችን በማወዳደር የትኛው የተሻለ ውጤት እንዳመጣ test ማድረግ ያስችላል።
⚫Placement Control፦ ማስታወቂያው የት ቦታ (ለምሳሌ፡ Facebook Stories, Instagram Reels, Messenger ወዘተ) መታየት እንዳለበት መወሰን እንችላለን።

ጉዳቶች
⚫ውስብስብ ነው፦ ለመልመድ የተወሰነ ጊዜ እና ስልጠና ይፈልጋል።
⚫Setup ጊዜ ይወስዳል፦ ማስታወቂያውን ለማዘጋጀት፣ ፅሁፍ እና ዲዛይን ለመስራት ጊዜ ይፈልጋል።
⚫ከፍተኛ በጀት ይጠይቃል፦ ማስታወቂያው ውጤታማ እንዲሆን የተሻለ በጀት መመደብና በጥንቃቄ መከታተል ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ
ዓላማችሁ ፖስታችሁ ለብዙ ሰው እንዲደርስና ላይክ/ኮሜንት እንዲያገኝ ከሆነ Boost ማድረጉ ይበቃል። ነገር ግን ቀጥተኛ ሽያጭ፣ የደንበኛ መረጃ (Leads) ወይም ትልቅ Business ማሳደግ ከፈለጋችሁ Ads Campaign መጠቀም የግድ ይላል።


Facebook and TikTok ad ማሰራት የምትፈልጉ inbox አድርጉልኝ።

@mif_gfx
August 30, 2026 34 1