በነገራችን ላይ…ሲደወል የማታነሱለት፣ መልእክቱ የማይገዳችሁ፣ በቅን ልብ ለሚቀርባችሁ ሰው ፊት የምትነሱት ሁሉ… — Mirjan Digital — TG.ME

በነገራችን ላይ…ሲደወል የማታነሱለት፣ መልእክቱ የማይገዳችሁ፣ በቅን ልብ ለሚቀርባችሁ ሰው ፊት የምትነሱት ሁሉ ትዕግስቱ የማያልቅ እንዳይመስላችሁ።

አንድ ቀን ይመጣል—ያ የናቃችሁት ሰው ልክ እንደናንተ ዝምታን ይመርጣል። ጥሪያችሁን እያየ ያልፋል፤ መልእክታችሁን ችላ ይላል፤ ፊቱን ያዞራል።

ሰዎች አለመፈለጋቸውን ሲረዱና ክብራቸው ሲነካ ዞር ብለው የማያዩ ጨካኝ ለመሆን አያመነቱም። ያኔ እናንተም ፈላጊ ትሆናላችሁ፤ የሰለቻችሁ ድምፅ ይናፍቃችኋል፤ የናቃችሁት ትኩረት ይርቃችኋል።

ስለተወደዳችሁ አትኩሩ፤ ስለተፈለጋችሁም አትዘንጡ። የማንኛውም ሰው ትዕግስት ወሰን አለው።
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
August 28, 2026 34