በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ማኅበር እና ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ማኅበር የዳሬይክተሮች ቦርድ ተወካይ ተፈራ ተስፋዬ ባደረጉት ንግግር፣ መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ እዚህ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ለሌሎች መሰል ተቋማት ትልቅ አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን በመጥቀስ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚሁ ታሪካዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ማክሮፋይናንስ ተቋማት ማኅበር፣ የፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ የቦርድ አባላትና ማኔጅመንት፣ ጥሪ የተደረገላቸው ተቋማት፣ በርካታ የክብር እንግዶች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ታድመዋል።
ይህ ሁነት ተቋሙ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ መሸጋገሩን ያረጋገጠ ከመሆኑም በላይ፣ በሀገሪቱ የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥና የካፒታል ገበያ ማዕቀፉን ለማጠናከር የሚጫወተውን ሚና ጎልቶ ያሳየ ሆኖ ተጠናቋል።
መባዕ ማይከሮ ፋይናንስ ቀዳሚ የፋይናንስ አጋርዎ!
Follow Us
Website |Twitter(X) | TikTok | Facebook | Telegram Group | Telegram channel


















