. የዕለቱ መልዕክት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም ዘዳ 33 ሙሴ ሳይሞት እስራኤልን ሰብስቦ ይባርካቸውል ሙሴ ከጠበቀው ተስፋ ካደረግው ከዚያች ምድር ሳይደርስ ሊሞት የመጨረሻ ጊዜው ላይ እጁን ዘርግቶ ባረካቸው ከዚያን እንዲህ አለ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው እስራኤል መኖሪያው ምድረበዳውን አቋርጠው የሚደርሱበት ሀገር ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሆነ ነገራቸው በተሳካልን ነገር ብቻ ሳይሆን ባልሆነልንም ነገር ላይ እንዲህ ብለን እንደ ሙሴ እናውጅ ለእኛ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም -መልካም ቀን- @Markengeta @Markengeta
98
30
11
5
2
1August 27, 2026 8.2K 15 21