ታላቁን የእግዚአብሔርን ስራ በምስጋና አውጃለሁ!
Don't Show Your next Move!
"ሁሉም ሰው 'አትችልም' ባለበት፣ እኔ 'እችላለሁ' ብዬ የተነሳሁበት ጊዜ።"
2016 ዓ.ም ክረምት ላይ GAT ፈተና ወሰድኩ አለፍኩ ተቀጥሬም የራሴንም ስራ እሰራ ነበር በዚህ ሁሉ መሃል 24 ሰዓት በቀን አለኝ ቢዬ ማይጠቅም ጓደኝነት፣ ፊልም፣ ኳስ፣ መዝናኛ እና ሶሻል ሚዲያ ስክሮል... ጊዜን የሚበሉትን ሁሉ በሰላም ተሰናብቼ፣ ስራዬ ላይ ብቻ ፎከስ በማድረግ ህይወቴን በራሴ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ወሰንኩ። አንዳንዶች "አንዱን እንኳ አትጨርስም፣ አርፈህ ስራህን ስራ" በማለት ተስፋ ለማስቆረጥ ሞክረዋል። እኔ ግን የተማርኩትን Time Management ጥበብ ተጠቅሜ፣ ሁለት የሁለተኛ ማዕረግ (Master’s) ትምህርቶችን በአንድ ጊዜ በመጀመር ወደ አዲስ ፈተና ገባሁ።
መንገዱ ቀላል አልነበረም፤ እያንዳንዱ ቀን ትልቅ ትግል ነበረበት። ነገር ግን ዛሬ፣ እግዚአብሔር በአይኔ እያየሁ ጠላቶቼን ዝም አሰኝቶ የመጀመሪያውን ማዕረግ በክብር አስጨረሰኝ። አምናለሁ፤ ይህን የጀመረልኝ አምላክ፣ የጀመርኩትን ሁለተኛውንም ማዕረግ በድል ያስጨርሰኛል።
ዛሬ በሕይወቴ ውስጥ በጣም ልዩ የሆነ 1 ምዕራፍ ተጠናቋል። መማር እና ትምህርት ባያልቅም ላለፉት 2 ዓመታት ጊዜያት ውስጥ በርትቼበት የነበረውን የፕሮጀክት ማኔጅመንት የሁለተኛ ድግሪ(Master’s) ትምህርቴን በፈጣሪ ቸርነት አጠናቅቄያለሁ። ይህ ጉዞ የራሴ ጥረት ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ እርምጃ የሰጠኝ ጥበብ፣ ጽናት እና ያልተለየኝ ምሕረት ውጤት ነው።
ይህ አዲስ ምዕራፍ ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋ ለቆረጡ ሁሉ ትምህርት ነው። ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!
መዝሙረ ዳዊት 20:5 እንዲህ ይላል፡-
“በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።”
አዎን፣ የመልካምነቱ መታሰቢያ በዚህ ምዕራፍ ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊትም ለምመራቸውና ለምሳተፍባቸው ፕሮጀክቶች ሁሉ መሠረት ይሁንልኝ። ይህ ሂደት ቀላል አልነበረም፤ ነገር ግን ፈጣሪ ባይረዳኝ ኖሮ ዛሬ እዚህ መድረስ አይቻልም ነበር።
በዚህ የትምህርት ሂደት ውስጥ ለጎኔ ለቆማችሁ፣ ለጸለያችሁልኝ፣ ለተባበራችሁኝ ቤተሰቦቼ፣ ወዳጆቼ እና የስራ ባልደረቦቼ በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ይህ የአዲስ ጉዞ መጀመሪያ ነው፤ ለቀጣዩ ምዕራፍ ጌታም ይርዳኝ።
ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን!
#mebratelias #mabitech #mekore
23
2July 12, 2026 1.7K 2




