ከፈጣሪ ቀጥሎ የህይወቴ ብርሃኖች!
በዚህች አለም ላይ ስኖር ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ፣ ብዙ ውጣ ውረዶችንም አሳልፌያለሁ። ነገር ግን በሁኔታዎች የማይለወጥ፣ በጥቅም የማይደለል እና እኔነቴን ሳይሰለቹ የተሸከሙ ሁለት ታላቅ ባለውለታዎች አሉኝ፤ እነሱም እናቴ እና አባቴ ናቸው።
ለእናቴ(B)፦
የእኔ አለም መጀመሪያ፣ የፍቅር ትርጉም እና የትዕግስት ተምሳሌት የሆንሽው እናቴ ሆይ... እኔ እንድቆም አንቺ ጎንብሰሻል፣ እኔ እንድ ስቅ አንቺ እንባሽን አፍስሰሻል፣ እኔ እንድጠግብ አንቺ ጦምሽን አድረሻል። የከፈልሽው መስዋዕትነት በቃላት የሚገለጽ ባይሆንም፣ ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረቱ ያንቺ ጸሎትና ያንቺ መካሪነት ነው።
ለአባቴ(E)፦
የማከብረውና የምኮራብህ አባቴ ሆይ... የኑሮ ውጋት ሳይበግርህ፣ የህይወት አቀበት ሳይዝልህ ለእኔ ስትል የከፈልከው የጉልበት እና የልብ ዋጋ ዛሬም ድረስ በውስጤ ትልቅ ቦታ አለው። ካንተ የተማርኩት ጥንካሬ እና ስነ-ምግባር በየትኛውም ቦታ በኩራት እንድራመድ አድርጎኛል።
ለሁለታችሁም፦
ከፈጣሪ ቀጥሎ ለዚህች ህይወቴ ትልቁን ድርሻ የምትወስዱት እናንተ ናችሁ። “ልጄ ደስ ይበለው” በሚል ሃሳብ ብቻ የገዛ ህይወታችሁን መሰዋዕት አድርጋችሁ እዚህ አድርሳችሁኛል። ዛሬ ላደረጋችሁልኝ ሁሉ ምስጋናዬን ለማቅረብ ቃላት ቢያጥሩኝም፣ ፍቅሬ እና ክብሬ ግን ከሰማይ በላይ የገዘፈ ነው።
ፈጣሪ እድሜና ጤና ይስጣችሁ። የእናንተ ደስታ የእኔ ሰላም ነው፣ የእናንተ መኖር ለእኔ ብርታቴ ነው። ሁሌም እወዳችኋለሁ!
#Family #ParentsLove #Gratitude #MotherAndFather #Blessing #EthiopianFamily #Love #mabitech

20
5April 30, 2026 2.6K 3