ማስታወቂያ
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል። ሆኖም አንዳንድ ክልሎች ዘግይተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በመልቀቃቸውና በኢንተርኔት ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በመኖራቸው ምዝገባው እስከ ነሃሴ 20/2018 ደረስ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✅ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 80 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት
✅ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነቶች 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች፤
መሆኑን በድጋሚ እያስታወስን በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።