ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ምዘና 1ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ባካሄደው የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ምዘና፣ ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በከተማዋ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መካከል የ95.4 ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃን በመያዝ የላቀ ውጤት አስመዝግቧል
ይህ የተመዘገበው ድል ኮሌጁ ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ያስመዘገበውን የላቀ ደረጃ ያስጠበቀበትና ስኬቱን ዳግም ያረጋገጠበትሲሆን፣ የመሪነት ሚናውን በመወጣት በቴክኖሎጂ፣ በጥራት እና በስልጠና አሰጣጥ ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን እያካሄደ መሆኑን ማሳያ
ነው።
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተኩ ታዬ ለተመዘገበው የላቀ ስኬት ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትአስተላልፈዋል።
ዲኑ በመልዕክታቸው
ይህ የ2018 በጀት ዓመት ታሪካዊ ድል ሁላችንም እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነን ለጥራት፣ ለልህቀት እና
ለተቋማችን ዕድገት የከፈልነው የጋራ ላብ፣ ጥረት እና የትጋት ፍሬ ነው
ያሉ ሲሆን፣ በ2019 በጀት ዓመትም የተገኘውን አንጸባራቂ ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠልና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተለመደው የጋራ ስራና የባለቤትነት ስሜት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በዚሁ እለትም የኮሌጁ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው የ2018 የስራ አፈጻጸም ምዘና ከኮሌጆች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ በመሆን የኮሌጁን ደስታ እጥፍ ድርብ አድርጎታል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!

















