90's Music With Lyrics: post #360 — TG.ME

🎤 ድምፃዊ _ ተመስገን ታፈሰ 🎵(ተመለሺ) የተፈራ ነጋሽን Lyrics Written  By Fira 💚💛❤💚💛❤💚💛❤ ግፍ የዋልሽው በፍቅር ላይ አልዳኝም እምቢ ብለሽ ጭንቅ ጥብብ ባር ባር ሲለኝ በሃዘን እንባ የሸኘሁሽ ኧረ ነይ ተመለሽ ተይ ነይ /ከበደልኩሽ ካስቀየምኩሽ ይፈረድ ልካስሽ/2x ኧረ ነይ ዙሪያው ገደል ሆኖ ተስፋ በሌለበት ኑሮ እንዴት ይቻላል ኡሁሁ...ለመጪው ነው ማሰብ ያለፈውን ትተን መስማማት ይሻላል እስኪ ፍቅሬ ነይ እንተማመን ከኔ ወይስ ካንቺ የት ነው ያለው ስዕተት መሀላችን ፍቅር ሰላም ይውረድ በንፁህ ልባችን እንማከርበት እኔማ ያላንች መች ይሆንልኛል ሀሳብ እያጉላላ ያወዛውዘኛል ርቀሽኝ ስትሄጅ ርቀሽኝ ሄደሽ /ጨንቆኛል ጠቦኛል ከፍቶኛል/2x እስኪ ተረጅው ካጀማመሩ በመሰረቱ እንደሚለያይ በብዙ አይነቱ የሰው ፍጥረቱ በአለም የለም የማይሳሳት ልማጸንሽ ብበድልሽም ይቅር በይና ነይ ተመለሽ /ተመለሺ ተይ ተይ ተመለሺ ተይ ተይ/2x ግፍ የዋልሽው በፍቅር ላይ አልዳኝም እምቢ ብለሽ ጭንቅ ጥብብ ባር ባር ሲለኝ በሃዘን እንባ የሸኘሁሽ ኧረ ነይ ተመለሽ ተይ ነይ /ከበደልኩሽ ካስቀየምኩሽ ይፈረድ ልካስሽ/2x ኧረ ነይ ውል አልይዝም አለኝ ኑሮዬ ፈር አጣ ተመሠቃቀለ ስትለዪኝ ጎኔን ሀዘን ጎዳው ፍቅር ጎደለብኝ ገላዬ አንችን አለው ያለፈውን ትተን ተወቃቅሰን እንስማማ ይቅር እንባባልና ተመለሽ ይዘሽ ደግ ደጉን እኔም ማሪኝ ልበል የወደቀው ይቅና እኔማ ያላንች መች ይሆንልኛል ኑሮ እንደ ተራራ ገደል ሆኖብኛል ርቀሽኝ ሄደሽ ስንሰነባበት /ጨንቆኛል ጠቦኛል ከፍቶኛል/2x እኔስ እስካሁን ከውጣውረድ አልተለየሁም ሰላሙን ያጣ ያልተመቸው ሰው አደብ የለውም ምትክም የለኝ አንችም ጨክነሽ ሸሽቼሻለሁ 💚💛❤💚💛❤💚💛❤ Fira Music Lyrics @90's Music with lyrics ሼር➠

👍66❤37🥰4🔥3😱2😁1🤔1🫡1
November 3, 2023 44.4K 343