🎤 ድምፃዊ_ኤፍሬም_ታምሩ 🎵እስከ_መቼም_አልረሳም Lyrics Written By Fira 💚💛❤💚💛❤💚💛❤ እስከ መቼም አልረሳም ያንቺን ፍቅር እኔ እስከ መቼም አልረሳም ያንቺን መውደድ እኔ እስከመቼም አይጠፋ ያንቺ ናፍቆት ካይኔ ምርጫም የለው ጎኔ ሌላም አላውቅ እኔ አንቺው ነሽ ወገኔ 2x ዓለሙ ጨላልሞ ጠፍተሽ ጀምበሪቱ ኮከቡንም ጭኖ ነግሶብኝ ሌሊቱ እንደንጋት ሆነሽ ጎህ ሣትፈነጥቂ በውበትሽ ብርሃን ደጅ ሳታደምቂ ካለሁበት ሣትመጭ ወደኔ ሳትዘልቂ ቀን ይወጣል ብለሽ ከቶ እንዳትጠብቂ ኦሆ......... [አይጣል መውደድ አይጣል ፍቅር]፪x [አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል ፍቅር]፬x ችዬው ልክረም እንጂ ዓመትም መንፈቅም ኑሮውስ ያላንቺ ከቶ አይጣፍጥም አይጣፍጥም! አይጣፍጥም! አይጣፍጥም አይጣፍጥም! አይጣፍጥም! አይጣፍጥም እስከ መቼም አልረሳም ያንቺን መውደድ እኔ እስከ መቼም አልረሳም ያንቺን ፍቅር እኔ እስከመቼም አይጠፋ ያንቺ ናፍቆት ካይኔ ምርጫም የለው ጎኔ ሌላም አላውቅ እኔ አንቺው ነሽ ወገኔ 2x ዋለለ ባዘነ ልቤ ተንገላታ ቀልቤም ተሸነፈ አካሌም ተረታ ሆዴ እንደ ጠፍ መሬት ባንቺ እየታረሰ የዘራሽው ሥጋት ቡቃያው ደረሰ ኑሮዬ በሀሳብ እየደፈረሰ ሳገኝሽ የካብኩት ስለይሽ ፈረሰ ባንቺ ሃሣብ ፈረሰ ደስታዬ በሀዘን እየረሰረሰ የወጠንኩት ሁሉ ባንቺ ሀሳብ ፈረሰ: ኦሆ.........አይጣል መውደድ አይጣል ፍቅር አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል መውደድ አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል ፍቅር አይጣል አይጣል አይጣል አይጣል ፍቅር:: ችዬው ልክረም እንጂ ዓመትም መንፈቅም ኑሮውስ ያላንቺ ከት አይናፈቅም አይናፈቅም! አይናፈቅም! አይናፈቅም አይጣፍጥም! አይጣፍጥም! አይጣፍጥም 💚💛❤💚💛❤💚💛❤ Fira Music Lyrics @90's Music with lyrics ሼር➠
90's Music With Lyrics: post #348 — TG.ME
September 9, 2023 39.6K 195