@linkbiruk21b · 170 subscribers
𝓷𝓸 𝓹𝓪𝓲𝓷 𝓷𝓸 𝓰𝓪𝓷
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/linkbiruk21bIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created July 24, 2024per Telegram
We have been tracking it since August 25, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
ውሰደን እንዳንል ቅጣትህ አስፈራን፥ አኑረን እንዳንል ኖረን ምን አፈራን፥ ፀሎቱ ጠፍቶናል በፈለከው ምራን።
ነገን ኑረን ፥ ዛሬን ሞትን ትላንትናን እየለፋን ፥ በቀደም 'ለት ተቀበርን መሞቻና መሰንበቻው ፥ ሳይታወቅ የውል ፍቺው ቀን ልንጨብጥ በቀናችን ፥ ቀን አስጣለን መኖራችን።
እኔስ ኖሬዋለው ሲከፋኝ ሲደላኝ ከንግዲ ተወልዶ ሰው ለሚሆን ይብላኝ.
ተይው እንተወው ተይው እንተወው፤ ..... የዘመን ቃፊሩን ማለፍ አልቻልንና ይህ አለም ጥበቱ አልመጠነንና፤ ተይው እንተወው፤ ..... ውጥኑ ግብ ይሁን ጅማሬው ፍፃሜ፣ ቅፅበቷ ሙሉ እድሜሽ ወቅቷ ዘላለሜ።
እንደሰበዓሰገል ፡ ኮከብ ፡ ምሪት እንደመከተል – የሰጠሽኝ ፡ ምልክት የዐይንሽ – የቃልሽ ፡ ምሥጢር ለዛኔው ፡ እኔ ፡ ቢጠጥር ፤ ሳይገባኝ ስቀቴ ፡ እንደመራኝ ወርቅሽን ፡ በሰም ፡ ፈክሬ ሲገባኝ እሳቱ ፡ ተረፈኝ ፡ ዛሬ ። ለካ… ወደድኩሽ ፡ ብዬ ፡ ስመናቀር ሞትኩልህ ፡ ብለሽኝ ፡ ነበር ።