የልብ ቃል 🪓🛡️
ሀናን ጸጥ ያለች፣ ሰውን የማታስቸግር ወጣት ነበረች። በየቀኑ ወደ ቤተ መጻሕፍት ትሄድ ነበር። አንድ ቀን በዚያ የምታየው ወጣት አሚን ዓይኗን ሳያውቅ ልቧን ነካው። አሚን ትሁት፣ ጨዋ እና እምነቱን የሚጠብቅ ሰው ነበር። ሁለቱም እርስ በርስ ይወዳድዱ ነበር፣ ግን ያንን ስሜት በራሳቸው መንገድ ለመግለጽ አልፈለጉም። ሁለቱም "አላህ ከፈቀደ በሁሉ መንገድ እንገናኛለን" ብለው ይጠብቁ ነበር። ⚔️
ወራት አለፉ። አንድ ቀን አሚን ቤተሰቦቹን ይዞ ወደ ሀና ቤት መጣ። ለጋብቻ ጠየቃት። ሀና ከደስታ የተነሳ እንባዋን መቆጣጠር አልቻለችም። የኒካህ ቀን ደረሰ። አሚን ለሀና እንዲህ አለ፦ "ውበትሽን ሳይሆን ዲንሽን ወደድኩ፤ አላህን ስለፈራሽ አከበርኩሽ። ዛሬ አላህ የታገስነውን በሁሉ ሰጠን።" 🏰
ሀናም ፈገግ ብላ፦ "እውነተኛ ፍቅር ትዕግሥትን፣ እምነትን እና አላህን መፍራትን ይፈልጋል።"
ከዚያ በኋላ በመዋደድ፣ በመከባበር እና በአላህ መታዘዝ ተሞላ። ችግር ሲመጣ አንዱ ለሌላው ድጋፍ ይሆን ነበር፣ ደስታ ሲመጣም አላህን ያመግኑ ነበር።
መልእክቱ: እውነተኛ ፍቅር በመልክ ሳይሆን፤ በእምነት፣ በመከባበር እና በትዕግሥት ይጸናል። 🛡️🔥
2July 31, 2026 274 1