ተማሪ ሆኖ ከጎን ለጎን ስራ መስራት እንደሚባለው ቀላል አይደለም! እኔ አብዛኛውን የግቢ ህይወቴ በስራ ነው…

ተማሪ ሆኖ ከጎን ለጎን ስራ መስራት እንደሚባለው ቀላል አይደለም!

እኔ አብዛኛውን የግቢ ህይወቴ በስራ ነው ያሳለፍኩት ማለት ይቻላል እና ከትምህርት ጎን ለጎን ስራ መስራት ምን እንደሚመስል በደንብ አውቀዋለው ስለዚህ አሁን ምነግራችሁ ነገር ከግምት ወይም ከንባብ የመጣ ሳይሆን ከልምድ ነው!

በዚህ ዘመን “ university ሆኖ ከትምህርት ጎን ለጎን ስራ መስራት ያስፈልጋል? “ በሚል topic ማውራት የበራን ፀሀይ በጥላ እንደማሳየት ነው…ጉዳዩ “መስራት ያስፈልጋል?” ከሚለው “ምን መስራት ይሻላል?” ወደሚለው ከተዘዋወረ ቆይቷል..እኔ ደሞ ሁሌም እንደምለው በዚህ ግዜ university ሆኖ upfront capital የሚጠይቅ business ውስጥ መግባት ትክክለኛ ምርጫ ነው ብዬ አላስብም…ማቶከር የሚኖርባችሁ ያለምንም / ትንሽ / መነሻ ገንዘብ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎችን ነው…እንደነዚህ አይነት ስራዎች ደሞ ከናንተ በዋነኝነት ሚፈልጉት ግዜያችሁን ነው

እኔ ግቢ እያለው ብዙ ስራዎችን ብሰራም በዋነኝነት ትኩረት ሳደርግ የነበረው content creation እና SMM ( ልወጣ አከባቢ ) ላይ ነው…እና ሁለቱም ስራ ግዜያችሁን እንጂ መነሻ ገንዘብ አይጠይቁም በእርግጥ ከሁለቱም ውጭ በጣም ብዙ መነሻ የማይጠይቁ ስራዎች ቢኖሩም እኔ ስለማውቀው እና ስለሰራሁበት ብቻ ነው ማውራት የሚኖርብኝ

እና ፍላጎታችሁ ከሁለቱ አንዱ ከሆነ ( smm and content creation ) እነዚህን ስራዎች እንዴት መጀመር እንደምትችሉ ቀለል ያለች beginner roadmap በpdf መልኩ ተዘጋጅቶላቹሀል ከዚህ ፅሁፍ ስር አስቀምጬዋለው..አውርዳችሁ ተመልከቱት ጥያቄ ካላችሁ comment ላይ አስቀምጡልኝ✍️
🔥6❤1💯1
3 ноября 2026 г. 601