ድንቄም መዘመን🫤
በዚህ ግዜ ‘መዘመን’ ብለው ያሳመኑን ነገር እና የሚያሳዩን ነገር እጅግ የሚያሳዝን እና የሰውን ልጅ እውነተኛ ማንነት የሚያቀጭጭ አደገኛ ነገር ነው…ግን ቆይ ሲጀመር መዘመን ማለት ራሱ ምን ማለት ነው?
ብዙዎቻችን መዘመን ሲባል የ Westernኦችን idea, culture, አለባበስ እና የአኗኗር ሁኔታ አምጥቶ እዚህ apply ማድረግ ነው ሚመስለን ነገር ግን Science እና Technology የሰው ልጅ የጋራ የዕውቀት ውጤቶች እንጂ የየትኛውም civilization cultural monopoly አይደለም…ቴክኖሎጂን መጠቀም ሌላ ነው የራስን ባህል,ሞራል እና ማንነት ጥሎ የሌሎችን የቤት ስራ መቅዳት ሌላ ነው! መዘመን ማለት አዲስ አእምሮ ይዞ ማሰብ እንጂ የሌሎችን ማንነት እንደ ልብስ መልበስ አይደለም…እዚህ ላይ በደንብ ሊሰመርበት ይገባል folks
እውነተኛ ዘመናዊነት ልክ ዛሬ እንደምናየው ኃይማኖትን እና መንፈሳዊነትን እንደ ኋላ ቀርነት አድርጎ የሚጥል አይደለም…እውነተኛ ዘመናዊነት ልክ ዛሬ እንደምናየው ህሊናን እና ሞራልን እንደ አሮጌ ዕቃ ወርውሮ “የሚጠቅመኝ ከሆነ ትክክል ነው” የሚል የ Utilitarianism ሀሳብ የሚነግስበት አይደለም…. እውነተኛ ዘመናዊነት ልክ ዛሬ እንደምናየው የሰው ልጅ ዋጋን በባንክ አካውንት እና በቁስ የሚመዝን አይደለም… እውነተኛ ዘመናዊነት ልክ ዛሬ እንደምናየው ሰዎችን በ social media አቀራርባለው እያለ እጅግ የሚያራርቅ እና Spiritual Void የሚፈጥር አይደለም!
ስለዚህ folks ዋና ሀሳቤ ምንድነው መሰላችሁ…‘መዘመን’ ሚባለውን ነገር ከ westerns and europes ጋር ማያያዛችንን እናቁም እና ትክክለኛ ‘መዘመን’ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት እንሞክር ሚል ሀሳብ ለማስተላለፍ ነው!
Memento vivere🫴

7
4
2
1
128 октября 2026 г. 608