ከባለጌ ልብ ውስጥ ቅንጣት ትህትና
ከትሁትም ሀሳብ ሚጢጢ ብልግና
ብታይ አይግረምሽ አለም ይህ ነውና
ቀኔንም በሙሉ
አኩኩሉ ስልሽ ትያለሽ አልነጋም
እኔስ ምኔ ሞኙ
ላልደረሰ ጸሎት ስለት አላስገባም
ስሜን አስጥተሽው ሁሉ እየዘገነ
ከራሴ መልክ በልጦ የሳልሽኝ ገነነ
የቀረቡኝ ሁሉ በእኔ ላይ በር ዘጉ
ማክበርሽ ባይደርሰኝ ተይ ናቂኝ በወጉ
ባትሰሚኝም እንኳን
ካየሁት ልንገርሽ አትታለይ በዓለም
ትናንትሽን እይው
የማለልሽ እንጂ የሞተልሽ የለም
እናንተ ጠቢባን
ትዝታን ስትስሉ ቀለሜን ተዋሱ
ተስፋ ስትነድፉ ከእኔ ገፅ ጥቀሱ
ስሙን እያላችሁ እውነት ስትዘግቡ
እኔን አዳምጡና ይሄን ቃል ከትቡ
ትናንቱን ያወቀ ነገውን አይንቅም
ማቀፍ የለመደ በቀላሉ አይወድቅም
ከትናንቴ ሳመልጥ ነገየ ሲርቀኝ
ጊዜ ይሉት ቀመር ዛሬ ላይ ሲያቆመኝ
ወድቆ መነሳቱን ተክኜበታለሁ
ሳይሸኙኝ መሄዱን እችልበታለሁ
ፀሀይ ሌት ይወጣል?
ጉጉት ቀን ያፈጣል?
እኮ ስታስቢው
ልቤስ ከዚህ ኋላ
ያንቺን ልብ ይመርጣል?
✍️ አቤኒ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


